Back
ከቀኒሳ በቀለና ኤሊውድ ኪፕቾንጌ ማን ፈጣን እንደሆነ ጥቅምት 4 በለንደን ማራቶን ይለያል ተባለ
Aug 8, 2020
ኢትዮጵያ ነገ ዜና ፡ – በጉጉት የሚጠበቀው የለንደን ማራቶን ከቀነኒሳ በቀለ እና ከኬኒያዊው ኤሊውድ ኪፕቾጊ ማን ፈጣን እንደሆነ የሚለይበት ተጠባቂ ውድድር ነው ተባለ።
በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 4 በሚካሄደው
በዚህ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ዳግም ሊሻሻልበት እንደሚችል ከወዲሁ ተገምቷል።
ስመ ገናናና ውጤታማ የሆኑት ሁለቱ አትሌቶች የዓለም የማራቶን ክብረወሰንን ለማሻሻል የሚያደርጉት አልህ አስጨራሽ ፉክክር በከፍተኛ ሁኔታ ተጠባቂ ሆኗል።
ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ እ.ኤ.አ 2018 በርሊን ላይ 2:01:39 ሰዐት በማስመዝገብ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገቡ ይታወቃል።
በተመሳሳይ ቀነኒሳ በቀለ እዛው በርሊን ማራቶን ላይ  2:01:41 ሰዐት በመግባት የኪፕቾጌን ክብረወሰን ለሁለት ሰከንድ ሳያሻሽል ቢቀርም ሁለተኛው ፈጣኑ የማራቶን ሰዐት ባለቤት ለመሆን ችሏል።
የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን 1፡00፡22 በማጠናቀቅ ፣  በሞ ፋራህ ተይዞ የነበረውን የቦታውን ክብረ ወሰን ማሻሻሉም አይዘነጋም።
በሁለቱ ፈጣን አትሌቶች መካከል የሚደረገው ተጠባቂው ውድድር፣ በትክክልም ፈጣኑ አትሌት ማን እንደሆነ የሚለይበት ከመሆኑ ጎን ለጎን ምርጥ የተባሉ የዓለማችን የስፖርት ስፖንሰር ሺፕ ካምፖኒዎች ከፍተኛ በስፖንሰር ሺፕነት የሚሳተፉበት ሆኗል።
በዚህ ውድድር አሸናፊ ለሆነው 313,000 ዶላር ለሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፤ የለንደን ማራቶን ውድድር ባለፈው ሚያዝያ ወር ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንዲዛወር ተደርጓል።
በለንደን ማራቶን በተለምዶ ከ 40 ሺኅ ሰው በላይ የሚሳተፍ ቢሆንም፤ በወረርሺኙ ምክንያት ታዋቂ አትሌቶች ብቻ እንደሚሳተፉ የለንደን ማራቶን አዘጋጆች ውሳኔ አሳልፈዋል።
1Shares
0Comments
0Favorites
6Likes
Say something to impress...
Loading...
Comments
Hot

No content at this moment.

Relevant people
Ethiopia Nege
9726 Followers
Ethiopian alternative Media outlet
Related