Back
በአማራ ብሄር ተወላጆች እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ እየተፈጸመ ያለዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቁም!!!
Aug 5, 2020
በህይወት አበበ መኳንንት E-mail- afomith@gmail.com
አንድን ሰውም ሆነ ቡድን በቋንቋው፣ በዘሩ፣ በእምነቱ ወይም በሌላ አንድ የሚያደርገው መመዘኛ ምክንያት ሌላ ወይም ሌሎች ሰዎች ወይም ቡድኖች ተነስተው፣ የአካላዊና ሞራላዊ ጉዳት ከማድረስ ጀምሮ እስከ ግድያ የሄደ ህገ ወጥ ተግባር የዘር ማጥፋት ወንጀል ተብሎ ይፈረጃል። ማንኛውም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርስ የጥፋት ድርጊት ወንጀል ተብሎ የሚፈረጅ ቢሆንም የዘር ማጥፋት ወንጀል ግን በቀጥታ ከጉዳዩ ምንም ግንኙነት የሌላቸው ንፁሃንን ሰለባ የሚያደርግ በመሆኑ ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል መሆኑን በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ አሕጉራዊና ብሄራዊ ህጎች ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።
ዲሴምበር 9/1948 ዓ/ም ፀድቆ ጃንዋሪ 12/1951 ተግባራዊ መሆን የጀመረው የዘር ማጥፋት ወንጀልን የመከላከል እና ፈፃሚዎችን ለመቅጣት የወጣውን ኮንቬንሽን ፈራሚ ከሆኑ ሃገራት ዉስጥ በቀደምትነት የምትገኘዉ ኢትዮጵያ እንደሆነች ይታወቃል። ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥበቃ የሚያደርጉ የአለም አቀፍ ስምምነቶችን የፈረመች ሀገር እንዲሁም በታሪኳ ከፖለቲካ አመለካከትና በጥቂቱ በአሕመድ ግራኝ ጊዜ ከነበረው የሃይማኖት መልክ ያለው ግጭት ውጭ በዘር ማጥፋት ወንጀል የማትነሳ ሃገር ሆና ብትቆይም ከቅርብ አመታት በኋላ ግን የዘር ማጥፋት ጭላንጭሎች መታየት የጀመሩ ቢሆንም በ2018 ዓ/ም ሚያዚያ ላይ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ግን ሰፊ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀልን የምታስተናግድ ሃገር ለመሆን ተገዳለች።
ሃገራችን ቀደም ሲል በፈረመቻቸው ስምምነቶች መሰረት መንግስት የዜጎችን ሰብአዊ መብት የማክበር፣ የመጠበቅ አና የማስጠበቅ ተቀዳሚ ሀላፊነት አለበት። ይሁን እንጂ መንግስት መሰረታዊና ተቀዳሚ የዜጎችን መብት ከማንኛውም አካላዊና ሞራላዊ ጥቃት የመከላከል ሃላፊንቱን በመዘንጋት በዕለት ተዕለት የታይታ ፖለቲካና የፕሮፓጋንዳ ስራ ላይ በመጠመዱ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተማዎች በርካታ ንጹሀን ዜጎች በብሄራቸዉ እና በሀይማኖታቸው (ኦርቶኦክስ ክርስትያን)  ከባድ ጥቃትና ጭካኔ የተሞላበት የግድያ ወንጀል ሲፈጸምባቸው ዝም ብሎ ከማየት ባሻገር ችግሩን ያነሱና የሞገቱ ሰዎች እንደ ሃሰተኛ የሚይታዩበትን ሁኔታ እንዲፈጠር በማድረግ መንግስታችን የወንጀል ተግባርን ባለመከላከልና ሲፈፀምም ባለማስቆም እንዲሁም ወንጀለኛን ተከታትሎ ለፍርድ ባለማቅረብ ሶስት ከባባድ ግድፈቶችን እየፈጸመ ከመሆኑም በላይ በድርጊት ትርጓሜ የወንጀል ተግባር ተባባሪ በሚያስመስለው ሁኔታ ውስጥ ይገኛል።
2Shares
1Comments
1Favorites
7Likes
Say something to impress...
Loading...
Comments
Hot

No content at this moment.

Relevant people
Zehabesha
6663 Followers
Latest Ethiopian News Provider
Related